በአማራ
ብሔራዊ ክልላዊ
መንግሥት
በንግድና
ኢንዱስትሪ ቢሮ የወጣ
ነዳጅ
በበርሜል አቅርቦት
ንግድ ሥራ የችርቻሮ
ዋጋ ትመና መመሪያ
ዘመናዊ
የነዳጅ ማደያ
ባልተቋቋመባቸው
ከተሞች ነዳጅ
በበርሜል እየተጓጓዘ
ለገበያ እየቀረበ
ይገኛል፡፡ ይህ
የነዳጅ ችርቻሮ ንግድ
ምንጩ አንድም
በአካባቢው ከሚገኙ
የነዳጅ ማደያዎች
ወይም ከዲፖ በሕዝብ
ማስታወቂያው
በተወሰነው ታሪፍ
መሠረት ከነዳጅ
ማደያዎች በተመጣጣኝ
ትርፍ ሊቀርብ
ስለሚገባው፣
ለሸማቹ
በበቂ መጠን
እንዲቀርብ በማድረግ
የኢነርጂ ፍላጐቱን
ከማሟላት ባሻገር
አንዳንድ በመስኩ
የተሰማሩ የንግድ
ድርጅቶችም የንግድ
ዕቃው የዋጋ ትመና
ወይም ታሪፍ
አለመወሰን በቅርበት
ሊያገኙ የሚችሏቸውን ደንበኞች
እያጡ በመሆኑ
የችርቻሮ መሸጫ ዋጋው
እንዲወሰንላቸው
ጥያቄ እያቀረቡ
በመሆኑ፣
ማደያ
ባልተቋቋመባቸው
አካባቢዎች ደረጃውን
በጠበቀ መለኪያ
እንዲሸጥ በማድረግ
ማደያ ካቋቋሙ ንግድ
ድርጅቶች ጋር ያለውን
ሕገወጥ አሰራር
በመከላከል ሕጋዊ
የንግድ ውድድር
እንዲሰፍንና
አቅርቦቱ እንዲሳለጥ
መደገፍና መከታተል
ስለሚገባ፣
በዚህም መሠረት ወጥ የሆነ መመሪያ መኖር ስለአለበት ነዳጅና የነዳጅ ውጤቶችን ታሪፍ ለመወሰን በየጊዜው በወጣው የሕዝብ ማስታወቂያ እና በክልሉ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ቁጥር 3/1990 ዓ/ም አንቀጽ 41 ድንጋጌ መሠረት የአብክመ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ “ ነዳጅ በበርሜል አቅርቦት ንግድ ሥራ የችርቻሮ ዋጋ ትመና መመሪያ ቁጥር 5 “ አውጥቷል፡፡
1.1 “ ነዳጅ
በበርሜል አቅርቦት ንግድ
“ ማለት ቤንዚንን
ሳይጨምር ናፍታና
ነጭ ጋዝን ወይም
ከሁለቱ አንዱን በበርሜል
የመነገድ ተግባር
ነው፡፡
1.2 “ የነዳጅ
መጠን መለኪያ “ ማለት
ነዳጅ በበርሜል ለሽያጭ
ሲቀርብ በጥራት ደረጃ
ባለስልጣን
የተረጋገጠ የነዳጅ
መሸጫ መለኪያ ማለት
ነው፡፡
1.3 ‹‹ የፍሳሽ
ጉድለት ›› ነዳጅ ከቦቴ
ወደ በርሜል እንዲሁም
ወደ ተለያዩ የነዳጅ
መያዣ ዕቃዎች
ሲገለባበጥ
የሚከሰትን የፍሳሽ
ጉድለት ወጪን ለማካካስ
የሚያዝ መጠን ነው፡፡
ሀ/
ነዳጅ ከተገዛበት
ከተማ ድርጅቱ
እስከሚገኝበት ከተማ
ድረስ ለተገዛው ነዳጅ
መጠን ብቻ በአካበቢው
ገበያ ዋጋ
የተጓጓዘበትና
የትራንስፖርት
ያገልግሎት ክፍያ
በወጪነት ይያዛል፡፡
ለ/
ከነዳጅ አከፋፋይ
ኩባንያ ወይም ከዘመናዊ
የነዳጅ ማደያ በሕዝብ
ማስታወቂያው ታሪፍ
ውሣኔ መሠረት ለተገዛ
ነዳጅ የተገዛበት
ዋጋ፣
ሐ/
ነዳጁን ከአከፋፋይ
ኩባንያው በፈሳሽ
ጭነት/በቦቴ እስከ
ንግድ ድርጅቱ
ሳይደርስ በተጨማሪ
ቀሪ ርቀት ወይም
ርቀቱን ሙሉ በሙሉ
በበርሜል ሲጓጓዝ
የአካባቢውን
የአገልግሎት ክፍያ
መሰረት ያደረገ
ለማስጫኛ ወይም/እና
ማራገፊያ የወጣ ወጪ፣
መ/
በአካባቢው ገበያ ዋጋ
መሰረት ለአጓጓዥ
ድርጅት ለማጓጓዣ
አገልግሎት የተከፈለ ክፍያ
፡፡
ሠ/
የማዘጋጃ
ቤት ቀረጥ
ይህ ወጪ
የንግድ ዕቃው
በሚጓጓዝባቸው
መስመሮች የሚገኙ የከተማ
አስተዳደሮች/ ማዘጋጃ
ቤቶች ሲጫን ወይም
ሲራገፍ ወይም ለተለዬ
ዓላማ ከንግዱ ጋር
በተያያዘ ምክንያት
የተከፈለ ክፍያ፣
ረ/
ከላይ ከ‹‹ሀ››
እስከ ‹‹ሠ››
የተዘረዘሩት ሁሉም
ሕጋዊ ደረሰኝ ሊቀርብ
ይገበዋል፡፡
ሰ/
በሕጉ መሰረት የሽያጭ
ታክስ ተጨማሪ ሆኖ
የሚያዝ ይሆናል፡፡
ሸ/
የፍሳሽ ወጪ
1. የፍሳሽ
ጉድለት ወጪን
ለማካካስ ከቀረበው
የነዳጅ መጠን 0.2% /ዜሮ
ነጥብ ሁለት/ የሚያዝ
ይሆናል፡፡
አስረጅ፡- የንግድ
ድርጅቱ 10,000 ሊትር
አጓጓዘ ቢባል ለዚህ
የፍሳሽ መጠኑ የሚሰላው
10,000 x 0.2% = 20 ሊትር ይሆናል
ማለት ነው፡፡
2. የመጣው
ነዳጅ መጠን
በበርሜልና በደረሰኝ
የተገለፀው መጣጣም
አለበት፡፡
3. የፍሳሽ
መጠን ከታወቀ በኋላ
ተገዛ ተብሎ ደረሰኝ
ከቀረበበት ነዳጅ አከፋፋይ
ኩባንያ ወይም ከነዳጅ
ማደያ ከተገዛበት ዋጋ
ተባዝቶ የተገኘው ዋጋ
እንደ ወጪ ተይዞ
የሚሰላ ይሆናል፡፡
አስረጅ፡-
በባ/ዳር ከተማ
ከማደያ የናፍጣ መሸጫ
በሊትር ብር 5.50፣
-
10.000
ሊትር ተጓጓዘ ቢባል፣
-
የፈሳሽ
መጠኑ 10,000 x 0.2% = 20 ሊትር፣
-
የፈሳሽ
ወጪ መጠን
20 ሊትር x 5.50 ብር/ሊትር = 110
ብር ይሆናል ማለት
ነው፡፡
ቀ/
ያልተጣራ ትርፍ
ከላይ ከተዘረዘሩት
ወጪዎች ያልተካተቱ
ልዩ ልዩ የጉዞ
ወጪዎች፣ የትርፍ
መጠን… ወዘተ
የሚሸፈኑበት
ከጠቅላላ ወጪዎች በተጨማሪ
ለሊትር 7
/ሰባት/ ሣንቲም
ተጨማሪ ተደርጐ
የሚያዝ ይሆናል፡፡
በ/ የችርቸሮ ዋጋ
ተመን ማጠቃለያ ስልት
² የነዳጅ
መግዣ ዋጋ ብር ---------------------------- ሀ
² የማጓጓዣና
የትራንስፖርት ወጪ
ብር ------------- ለ
² የማስጫኛ
ወይም/እና የማራገፊያ
ወጪ ብር ------- ሐ
² የማዘጋጃ
ቤት ቀረጥ ብር
------------------------------- መ
² የፍሳሽ ወጪ
ብር -------------------------------------- ሸ
² ሽያጭ ታክስ
ብር …………………………….…… ሰ
ጠቅላላ
ወጪ ብር ድምር------------------- አ
² የተገዛው
ጠቅላላ ነዳጅ መጠን
በሊትር
---------- ወ
ስለዚህ
የአንድ ሊትር ችርቻሮ
መሸጫ ዋጋ ብር '' አ '' ሲካፈል '' ወ '' ተሰልቶ
የተገኘው ውጤት /ብር
ለሊትር/ ይሆናል
ማለት ነው፡፡
ተ/ ከላይ ከ‹‹
በ ›› የቀረበው የተመን
መጠን ማጠቃለያ ስሌት
ከፍተኛ
ጣሪያ ችርቻሮ መሸጫ
ዋጋ ተመን ሲሆን
ነጋዴው ከተመኑ በታች
መሸጥ ከፈለገ ዋጋውን
በጽሁፍ አሳውቆ መሸጥ
ይችላል፡፡ ሆኖም
በአካባቢው ካለ ማደያ
የመሸጫ ዋጋ ማነስ የለበትም፡፡
3.
ዘመናዊ
ነዳጅ ማደያ ባለበት
ከተማ በ30 ኪሎ ሜትር
ክልል የነዳጅ
በበርሜል አቅርቦት
ንግድ ሥራ ፈቃድም
ሆነ የነዳጅ ዋጋ
ትመና አገልግሎት
አይሰጥም፡፡
4. የነዳጅ
ዋጋ ተማኝ ኮሚቴ
ስለማቋቋምና
ተግባሩ፤
ሀ/
ኮሚቴው አምስት
አባላት ይኖሩታል፡፡
¨
ንግድና
ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት
ኃላፊ ------------------------------------------------
ሰብሳቢ
¨
ገንዘብና
+ላን ጽ/ቤት
---------------------------------------------------------------- አባል
¨
ከተማ
ማዘጋጃ ቤት/ከተማ
ቀበሌ ----------------------------------------------------
አባል
¨
የንግድና
ዘርፍ ማህበራት
ም/ቤት ወይም ዘርፍ
ማህበራት ም/ቤት---------- አባል
¨
ንግድና
ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት
የፍትሃዊ
ን/ማስ/የሥ/ሂደት
አስተባባሪ------
አባልናፀሐፊ
ለ/
ኮሚቴው በየጊዜው
የሚቀርቡለትን
ሰነዶች ሕጋዊነትና
ከአካባቢው ገበያ ዋጋ
ጋር
በማገናዘብ
በመመሪያው መሠረት
መርምሮ በዕለቱ የችርቻሮ
ዋጋ ተመን
ይወስናል፡፡
ሐ/
የተመን ውሣኔው
በቃለ-ጉባኤ መዝግቦ
ይይዛል፣ ውሣኔውን
ለአካባቢው
መንግሥታዊ መ/ቤቶችና
ድርጅቶች በሰብሳቢው
አማካኝነት በደብዳቤ
ያሣውቃል፣
መ/
የተወሰነውን
የችርቻሮ የተመን ዋጋ
በማስታወቂያ
ይገልፃል፤ በንግድ
ድርጅቱ ውስጥና በር
ላይ ለሸማቹ በሚታይ
ቦታ እንዲለጠፍ
ያደርጋል፣
ሠ/
የተወሰነውን ተመን
ስለመከበሩ ክትትል
ያደርጋል፣ ህገ-ወጥ
ድርጊት መፈፀሙ
ሲረጋገጥ ተገቢውን
አስተዳደራዊና ህጋዊ
እርምጃ ይወስዳል፣
ረ/
የነዳጅ ዋጋ ለውጥ
/መቀነስ ወይም
መጨመር/ በሕዝብ
ማስታወቂያ የሚገለጽበትን
ጊዜን በመከታተል
የወቅቱን የገበያ
ፍላጎት መሰረት
ያደረገ አቅርቦት
እንዲኖር በመስኩ
ለተሰማሩ ነጋዴዎች
ምክርና መረጃ በመስጠት
ይደግፋል፡፡
ሸ/
አሰራሩን በመገምገም
የተሻለ አሠራር
ይቀይሳል፤
አፈፃፀሙን
ለሚመለከተው ያሣውቃል፣
5. የነጋዴው
ግዴታ
ሀ/
ለገበያው በቂ የነዳጅ
መጠን በመያዝ ጥራቱን
የጠበቀና በህጋዊ መለኪያ
መሸጥ ይኖርበታል፣
ለ/
ስለአቅርቦቱና ሺያጩ
መረጃ ሲፈለግ
ተገቢውን ሕጋዊ ማስረጃ
የማቅረብ ግዴታ
አለበት፣
ሐ/
በተተመነው ዋጋ
መሠረት
ለሸማቾች/ለገዥዎች
እኩል አገልግሎት
መስጠት ይገበዋል፣
መ/ ሰለሥራው
እንቅስቃሴ ተገቢውን
ሪፖርት
ለሚመለከታቸው
አካላት በወቅቱ
ማቅረብ
ይኖርበታል፡፡
ሠ/
የተተመነው የችርቻሮ
ዋጋ ለሸማቹ በሚታይ
ቦታ መለጠፍ አለበት፣
ረ/ ለንግድ
ድርጅቱ ነዳጅ
እንዳቀረበ ተገቢውን
ሕጋዊ ማስረጃ
ለኮሚቴው በማቅረብ
ዋጋው እንዲተመንለት
ማድረግ
ይኖርበታል፡፡
6. የተሻሩ
መመሪያዎች፤
ይህን
የሚቃረን ማንኛውም
መመሪያ ይህ መመሪያ
ፀድቆ ከወጣበት ዕለት
ጀምሮ የተሻረ ነው፡፡
7. መመሪያው
የሚፀናበት ጊዜ፤
ይህ
መመሪያ በአብክመ
ንግድና ኢንዱስትሪ
ቢሮ ፀድቆ ከወጣበት
ዕለት ጀምሮ የፀና
ይሆናል፡፡
አብክመ ንግድና
ኢንዱስትሪ ቢሮ
ባህር ዳር