v ከ1985—2000 በክልሉ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ያወጡ ባለሀብቶች
በካፒታል 43480415001 በፕሮጀክት 3393 ::
v በክልሉ ባለፉት 4 አመታት ከ 146243 በላይ ወጣትና ስራ አልባ ወገኖች የስራ እድል አገኙ::
v በክልላችን በንግድ ስራ የተሰማሩ 91502 ነጋዲዎችና 1551548174 ካፒታል የሚያቀሳቅሱ ወገኖች በመስኩ ተሰማርተው ይገኛሉ::
v ባለፉት አመታት በክልሉ ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ወገኖች በቁጥር 45.08 ሚሊዮን ይደርሳል ይህም በመረጃ ልዉዉጥ & በሰርቪስ አገልግሎት & በእውቀት ማስተላለፍ የራሱን ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተረጋግጦል::
በአማራ
ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት የአበባ፣
አትክልትና ፍራፍሬ
ኤክስፖርት
ኢንቨስትመንት
የአፈፃፀም ጀረጃ
ወርክ ሾፕ
የክልሉ መንግስት
እየተመዘገበ ያለውን
ፈጣን ኢኮኖሚያዊ
እድገት ቀጣይነት
በማረጋገጥ የህዝቡን
የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል
የግል
ኢንቨስትመንቱን
ፍሰት በዓይነትና
በመጠን ለማሣደግ
ከፍተኛ እንቅስቃሴ
እያደረገ ይገኛል፡፡
በተለይ በአነስተኛ
መሬት ከፍተኛ ምርት
የሚያመርቱ በገበያ
ተፈላጊና በተነፃፃሪ
ከፍተኛ ዋጋ
የሚኖራቸውን
የኤክስፖርት ምርት
የሚያመርቱ፣ እንዲሁም
በርካታ የሥራ ዕድል
የሚፈጥሩ
የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን
በመጋበዝ፣
በመፍቀድና ልዩ ድጋፍ
በማድረግ እየተሠራ
ይገኛል፡፡
የአበባ፣
አትክልትና ፍራፍሬ
ኤክስፖርት
ኢንቨስትመንት ልዩ
ድጋፍና ትኩረት
ከሚሰጣቸው
የኢንቨስትመንት
ዘርፎች አንዱ ነው፡፡
ይህን ዘርፍ
ለማበረታታት ጠንካራ
የማበረታታት ኃይል
ያላቸው፣ ከፍተኛ የገንዘብ
ወጪ የሚጠይቁና
በቁጥርም በርካታ
የማበረታቻ
ዓይነቶችን ያካተተ
የማበረታቻ መመሪያ
ቁጥር 33/2000 በክልሉ
መስተዳድር ምክር ቤት
ተወስኖ ተግባራዊ
እየተደረገ ነው፡፡
1.
በባህር
ዳር 5 አካባቢዎችና
በደብረብርሃን 1
አካባቢ በድምሩ 811
ሄክታር የእርሻ መሬት
በብር 58,569,044.56 የማካካሻ
ካሣ ክፍያ ነፃ
በማድረግ ለ12
ፕሮጀክቶች በድምሩ 798
ሄ/ር መሬት የተፈቀደ
ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 387
ሄ/ር ለአበባ ልማት
እንደሁም 411 ሄ/ር
ለአትክልትና ፍራፍሬ
ልማት የሚውል ነው፡፡
2.
ለ11
ፕሮጀክቶች የጥልቅ
ጉድጓድ ውሃ የሙከራ
ቁፋሮና የውሃ መጠን
ልኬታ ሥራ ብር 3,641,956.38 ወጪ
የተደረገ ሲሆን
በዚህም ሙከራ በ9
ቦታዎች በቂ የመስኖ
ውሃ ማግኘት
ተችሏል፡፡
3.
የአካባቢዊና
ማህበራዊ ተጽእኖ
ግምገማ ጥናት በባህር
ዳር ዩኒቨርስቲ አማካኝነት
እየተጠና ሲሆን ጥናቱ
ከመንግስት በጀት ብር
371,294.00 የጠየቀና
በመስከረም/ 2002 ዓ/ም
መጨረሻ አካባቢ
እንደሚጠናቀቅ
ይገመታል፣
4.
የፕሮጀክቶች
እርሻ መሬት ድረስ
የኤለክትሪክ ኃይል
መስመር ለማዘርጋትና
የትራንስፎርመር
መሣሪያ ለማስተከል
ብር 1,447,563.78 ወጪ በማድረግ
አገልግሎቱ
እንዲቀርብ ክትትል
እየተደረገ ይገኛል፣
በተጨማሪም
5.
በፕሮጀክቶቹ
አካባቢ የተጠናከረ
የሰላምና ፀጥታ
ማስከበር ተግባራትና
ሌሎች አስፈላጊ
ድጋፎች እየቀረቡ
ሲሆን በጥቅሉ ቀጥተኛ
ያልሆኑ ወጪዎችን
ሳይጨምር ብር 64,029,858,.72
የክልሉ መንግስት ወጪ
በማድረግ የሚጠበቅበትን
ሙሉ በሙሉ በመወጣት
የፕሮጀክቶቹን ሥራ
መጀመር በመጠባበቅ
ላይ ይገኛል፡፡
II. በፌደራል
መንግስት ደረጃ
የሚቀርቡ
አገልግሎቶችን
በተመለከተ፡-
1.
በባህር ዳር
አየር ማረፊያ ተጀምሮ
የነበረውና በውጭ ምንዛሬ
እጥረት የተቋረጠው
የቀዝቃዛ መጋዝን (Cold Store)
ግንባታ ሥራ በአሁኑ
ጊዜ የተጀመረውና
ግንባታውን በፍጥነት
ለማጠናቀቅ ጥረት
እየተደረገ ይገኛል፣
2.
በግብርና
ሚኒስቴር የሚቀርበው
የፋይቶ እና የፋይቶ
ሳኒታሪ አገልግሎቶችን
ለመስጠት የሚያስችል
የሰው ኃይል ተካሂዶና
በባህር ዳር ከተማ ቢሮ
በመከራየት ዝግጅቱን
አጠናቋል፣
3.
የኢትዮጵያ
ልማት ባንክ 70-30 በሆነ
የብድር መዋጮ ብድር
ለመስጠት ተዘጋጅቷል፣
4.
በኢትዮጵያ
አየር መንገድ የሚቀርበው
የጭነት አውሮፕላን (cargo)
አገልግሎት
በፕሮጀክቶቹ ምርት
የማቅረብ ሂደት
የሚወሰን ሆኖ፣ የሚመረተውን
ምርት በሚመረጥ
መንገድ ማጓጓዝ
እንደሚቻልና ለዚህም
የሚረዳ ቅድመ
ዝግጅቶች
እንደሚደረግ ለማወቅ
ተችሏል እንዲሁም፣
5.
የብሔራዊ
ባንክ እና የጉምሩክ
አገልግሎቶችን
በተመለከተ የምርት
ማጓጓዙ ሂደት
ከመጀመሩ በፊት
በባህር ዳር የሚገኙ
መ/ቤቶቻቸውን
በማጠናከር
አገልግሎታቸውን
ማቅረብ እንደሚችሉ
ከየመ/ቤቶቹ የሥራ
ኃላፊዎች ማወቅ
የተቻለ ሲሆን የቅድመ
ዝግጅት ቀሪ ሥራ ያለባቸው
የፌደራል መ/ቤቶች
ከምርት አቅርቦት
በፊት
አገልግሎታቸውን ለማቅረብ
በሚያስችል መልኩ
የድርጊት መርሃ ግብር
እንዲያቀርቡና አፈፃፀሙን
በተመለከተ የጋራ
መድረክ (ወርክ ሾፕ)
እየተዘጋጀ
ለመገምገም የጋራ
ስምምነት
ተደርሷል፡፡
III. የፕሮጀክቶች
የአፈፃፀም ደረጃን
በተመለከተ፡-
|
1. |
ወደ
ግንባታ የገቡ
ፕሮጀክቶች ቁጥር ------------------------------------------- |
2 |
|
2. |
ለግንባታ
ሥራ የተሻለ ቅድመ
ዝግጅት በማድረግ
ላይ ያሉ------------------- |
3 |
|
3 |
በቅርቡ
መሬት የተረከቡና
አበረታች ሂደት ላይ
የሚገኙ---------------------- |
1 |
|
4 |
በኢትዮጵያ
ልማት ባንክ የብድር
ጥያቄ አቅርበው
ውሣኔ የሚጠባበቁ------- |
2 |
|
5 |
በሚጠበቀው
የአሠራር ደረጃ
እየሠሩ ያልሆኑ
ፕሮጀክቶች-------------------- |
2 |
|
6 |
ምንም
እንቅስቃሴ ያላሳዩ
ፕሮጀክቶች ቁጥር
---------------------------------- |
2 |
የፕሮጀክቶቹ የሥራ
አፈፃፀም ደረጀ
በተጠቀሰው መልኩ ሲሆኑ
የአበባ አትክልትና
ፍራፍሬ ምርት በበቂ
መጠን ለጭነት
አውሮፕላን ለማቅረብ
ሁሉን ፕሮጀክቶች
በተመሣሣይ ጊዜ ወደ
ምርት ማምረት ሂደት
እንዲሸጋገሩ
ለክትትል
እንዲያግዝም
የድርጊት መርሃ ግብር
እንዲያቀርቡና ወደ
ሥራ በማይገባ
ፕሮጀክት ላይ እርምጃ
እንዲወስድ እንዲሁም
ከፕሮጀክቶች ሥራ
መጀመር ጋር ተያይዞ
አቅም ባላቸው
ባለሃብቶች ዘርፋን የማስፋፋት
ጥረት እንዲደረግ
ስምምነት
ተደርሶበታል፡፡