የንግድ
ትርኢት የአፈፃፀም
መመሪያ
የኢፊዲሪ
መንግሥት በአሁኑ
ወቅት ከምታራምደው
የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ
ፖሊሲ ጋር የማጣጣምና
ለህጋዊ የንግድ ሥራ
እንቅስቃሴ ምቹ
ሁኔታዎችን ለመፍጠር
የሚያስችል የንግድ
ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ
ቁጥር 67/89 በማውጣቱና ይህን
አዋጅ መሠረት
በማድረግ የአማራ
ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት ምክር ቤት
የንግድ ምዝገባና
ፈቃድ ደንብ ቁጥር 3/9ዐ
አውጥቷል፡፡
በዚሁ
መሠረት የክልሉን
ተጨባጭ ሁኔታ
ያገናዘበና የሁሉንም
ተጠቃሚነት
በአረጋገጠ መልኩ የምርትና
የፈጠራ ሥራዎችን
ለማስተዋወቅ ፣
የኢንቨስትመንት
ዕድሎችን የሚዳስሱ
አማራጮችን
ለመፍጠርና የክልሉን
የኢንዱስትሪና
የእርሻ ምርታማነትን
ለማሻሻል፣
የቴክኖሎጅ ሽግግርን
የባህልና የሀሣብ
ልውውጦችን
ለማዳበር፣ ገቢያን
ለመሞከርና በምርት
ላይ ያተኮረ የሻጭና
የገዥ የአገልግሎት
አሰጣጥ ግንኙነት
አድማስንና ንግድን
ለማስፋፋት የሚያስችል
የንግድ ትርኢት
የአፈፃፀም መመሪያ
ማውጣት በማስፈለጉ፣
የአማራ
ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት ንግድና
ኢንዱስትሪ ቢሮ
በኢፊዲሪ የንግድ
ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ
ቁጥር 67/89 አንቀጽ 39 መሠረት
ይህን መመሪያ
አውጥቷል፡፡
ክፍል
አንድ
ጠቅላላ
አንቀጽ
1 አጭር ርዕስ
ይህ
መመሪያ “ በአማራ
ብሔራዊ ክልላዊ
መንግሰት የንግድ
ትርኢት ለማዘጋጀት
የወጣ የአፈፃፀም
መመሪያ” መመሪያ
ቁጥር ዐ2/99 ተብሎ
ሊጠቀስ ይችላል፡፡
አንቀጽ
2 ትርጓሜ
የቃሉ
አግባብ ሌላ ትርጉም
የሚያሰጠው ካልሆነ
በስተቀር በዚህ
መመሪያ ውስጥ
1. “ቢሮ”
ማለት በአማራ ብሔራዊ
ክልላዊ መንግስት
የንግድና ኢንዱስትሪ
ቢሮ ነው፡፡
2. ”የንግድ
ትርኢት” ማለት በዚህ
የአፈፃፀም መመሪያ
መሠረት ንግድን የማስፋፋት
ዓላማ ያለው ለተወሰኑ
ቀኖች ብቻ የንግድ
ዕቃዎችን
መሣሪያዎችን፣
የኢንዱስትሪና
የእርሻ ውጤቶችን፣
የፈጠራ ውጤቶችንና
ልዩ ልዩ
አገልግሎቶችን ወዘተ
ለህዝብ እይታ ወይም
ለሽያጭ በማቅረብ
የሚካሄድ ተግባር
ነው፡፡
3. “
ነጋዴ” የሚለው ቃል
በአዋጅ ቁጥር 67/89
አንቀጽ 2 ንዑስ
አንቀጽ 2 የተሰጠውን ትርጉም
ይይዛል፡፡
4. “
ሰው” ማለት ማንኛውም
የተፈጠሮ ሰው ወይም
በህግ የሰውነት መብት
የተሰጠው ድርጅት ነው
5. “
አዘጋጅ” ማለት
የንግድ ትርኢት
ለማዘጋጀት በዚህ
መመሪያ መሠረት ፈቃድ
የሰጠው ሰው ወይም
ድርጅት ነው፡፡
6. “ማመልከቻ”
ማለት በዚህ መመሪያ
መሠረት የንግድ
ትርኢትን ለማዘጋጀት
የሚቀርብ የጽሁፍ
ጥያቄ ነው፡፡
7. “
ፈቃድ” ማለት በዚህ
መመሪያ መሠረት
የንግድ ትርኢት
ለማካሄድ በቢሮው ለአዘጋጁ
የሚሰጥ የፁሁፍ
ማረጋገጫ ነው፡፡
8. “
ውል” ማለት የንግድ
ትርኢት ለማካሄድ
ፈቃድ የተሰጠው
አዘጋጅ ስለ ንግድ
ትርኢቱ አጠቃቀም
ሁኔታ የተዘረዘሩ
መብቶችና ግዴታዎችን
ለማክበር የተፈረመ
የስምምነት ሰነድ ነው፡፡
አንቀጽ
3 የአፈፃፀም ወሰን
ይህ
የአፈፃፀም መመሪያ
በአማራ ብሔራዊ
ክልላዊ መንግስት
ውስጥ የንግድ ትርኢት
በሚያዘጋጅ
ሰው/ድርጅት ላይ
ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ክፍል
ሁለት
አንቀጽ
4 ፈቃድ ሲሰጥ ሊሟሉ
የሚገባቸው
መመዘኛዎች /
መስፈርቶች/
አንቀጽ
5 የአዘጋጁ ግዴታዎች
አንቀጽ
6 የቢሮው ተግባርና
ኃላፊነት
አንቀጽ
7 በቢሮው ስለሚወሰዱ
አስተዳደራዊ
እርምጃዎች
አዘጋጁ
በመመሪያው
ከተመለከተው ውጭ
ትርኢቱን እያካሄደ
መሆኑ ሲረጋገጥ ቢሮው
ድርጊቱን በጥሞና
በመመርመር
የሚከተሉትን
እርምጃዎች ይወስዳል፡፡
አንቀጽ
8 ለትርኢቱ
ስለሚቀርቡ ዕቃዎች
በዚህ
መመሪያ መሠረት ከውጭ
አገር ለንግድ ትርኢት
የሚቀርቡ እቃዎች ለሽያጭ
ሣይሆን ለትይንት
የሚውሉ ከሆነ
መጠናቸው በየአይነቱ
v
ኤሌክትሮኒክስ
እቃዎች እስከ----------------------3
v
ሌሎች
በቁጥር የሚለኩ እስከ
--------------------5
v
በፖኬት
እስከ ---------------------------------------5
v
በኪሎ
ግራም /እሽግ/ እስከ
------------------------2 በኩንታል
v
በሊትር
እስከ ---------------------------------------- 2ዐዐ
ሊትር
ሆኖ
ለሽያጭ የሚቀርብ
ከሆነ ግን መደበኛውን
የውጭ ንግድን
በተከተለ መልኩ
ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
አንቀጽ
9 ስለንግድ ትርኢት
ፈቃድ ክፍያ
በዚህም
መመሪያ መሠረት
ለሚሰጥ የንግድ
ትርኢት ፈቃድ ብር
2ዐዐ /ሁለት መቶ /
ለቢሮው ይከፈላል፡፡
ክፍል
ሶስት
ልዩ ልዩ
ሁኔታዎች
አንቀጽ
1ዐ ፈቃድ ለመጠየቅ
የሚቀርብ ማመልከቻ
የንግድ
ትርኢት ለማዘጋጀት
የሚቀርብ ማመልከቻ
አንቀጽ 11
የንግድ ትርኢት
ስለማቋረጥ
የተከፈተው
የንግድ ትርኢት
ሊቋረጥ የሚችለው
በቢሮው ውሣኔ ብቻ
ይሆናል፡፡
አንቀጽ 12
ስለማሻሻል
ይህ
መመሪያ
እንደአስፈላጊነቱ
በቢሮው ሊሻሻል ይችላል፡፡
አንቀጽ 13
መመሪያው
ስለሚፀናበት ጊዜ
ይህ
የአፈፃፀም መመሪያ ከ
--------------------ጀምሮ የፀና
ይሆኖል፡፡